ወደ ዋናው ይዘት ይሂዱ

የአቤቱታ አቀራረብ ስርአት

የአቤቱታ አቀራረብ ስርአት

አቤቱታ ማለት በየደረጃው ላለው የፓርቲ መዋቅር ቅሬታ አቅርቦ በውሳኔው ባልረኩ አባላት ወይም አመራር ወይም አካላት በየደረጃው ላሉት የኮሚሽን መዋቅር የሚቀርብ አቤቱታ ነው

የአቤቱታ አቅራቢው የሚኖረው ግዴታ:
  1) አቤቱታውን በጽሁፍ ማቅረብ አለበት
  2) የአቤቱታ አቅራቢው ሙሉ ስም
  3) የአቤቱታው ጭብጥና የምቃወምበት ምክንያቶች
  4) የውሳኔ ግልባጭ እና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎች

ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ ለሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢውን የሰነድ ማስረጃዎች በተጠየቀ ጊዜ የማቅረብ ግዴታ አለበት

ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ የሚያቀርበው ሰነድ ህጋዊ ስለመሆኑ የማረጋገጥና በተጠየቀበት ጊዜ የማስረዳት ግዴታ አለበት

ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ ከራሱ የግል ፍላጎት በመነሳት የፓርቲውን ወይም አባል ወይም አመራር መልካም ስም በሚጎዳ መልኩ ለሚያቀርበው አቤቱታ በፓርቲው የዲስፕሊን መመሪያ ተጠያቂ ይሆናል

የአቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ:
  1) አቤቱታ አቅራቢው የሚቀርበው አቤቱታ ለአቤቱታ መነሻ የሆነ ውሳኔ ከሰጠበት ጊዜው አንስቶ ባሉት ተከታታይ ስድስት ወራት ውስጥ ማቅረብ አለበት
  2) ከተጠቀሰው ጊዜ አቤቱታውን ካልቀረበ አቤቱታው በይርጋ የታገደ ይሆናል

በአቤቱታ የማይታዩ ጉዳዮች:
  1) በይርጋ የታገዱ ጉዳዮች
  2) በፓርቲ መዋቅር ቅሬታው ቀርቦ ውሳኔ ያልተሰጠው ጉዳዮች
  3) በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ
  4) በፍርድ ቤት መብቱ የተገፈፈ አባል ጉዳዮች